TenaFirst - Agreement Application

የጤና ፈርስት የውል ስምምነት


 

May 27, 2026 ©

  , ኢትዮጵያ

 

ይህ ውል ስምምነት በአሐዱ ዌብ ዶት ኮም (ከዚህ በኋላ ጤና ፈርስት ተብሎ የሚጠራው) አድራሻው 22 ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ልዩ ስሙ ማሪያ ሮቫቶ ካቶሊክ ት/ቤት በሻ ህንፃ 3ኛ ፎቅ 310 ስልክ 0116 353516 email: contact@tenafirst.com የሕጋዊ ፍቃድ ምዝገባ ቁጥር የሆነው እና    (ከዚህ በኋላ አገልግሎት ተቀባይ ተብሎ በሚጠራው) አድራሻ:- /    ወረዳ    የቤት ቁጥር   ስልክ ቁጥር፡   ኢሜል   መካከል የተደረገ የውል ስምምነት የሚመለከት ነው ፡፡

አንቀጽ አንድ

የውሉ ዓላማ

1.  ጤና ፈርስት የድጅታል ቀጠሮ ማስያዣ ፕላት ፎርም በበይነ መረብ /Internet/ የጤና ተቋማትን የቀጠሮ አያያዝን አሁን ግዜው በደረሰበት የድጅታል ቀጠሮ ማስያዣ በመተግበር ቀላል፣ ቀልጣፋ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ የጤና ተቋማቶች እና አገልግሎት ፈላጊዎችን (ታካሚዎችን) በተቀላጠፈ መንገድ ለማገናኘት በማሰብ ለጤና ተቋም የድጅታል ቀጠሮ ማስያዣ ፕላት ፎርም አገልግሎት ለመጠቀም በቀን 2015 .ም ተስማምተው ይህን ውል ፈፅመዋል፡፡

አንቀፅ ሁለት

ትርጓሜ

2.1 በዚህ ውል ውስጥ በግልጽ ካልተጠቀሰ በስተቀር የሚከተሉት ቃላቶች እና አገላለፆች የሚከተለውን ትርጉም ይኖራቸዋል፡፡

2.1.1 “ውል" ወይም “ስምምነት" ማለት በውል ሰጪ እና በውል ተቀባይ መካከል የተደረገን ይህ ውል እና ከዚህ ውል ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሰነዶች እና በአባሪነት የተያያዙትን ሰነዶች ይጨምራል፡፡

2.1.2 “የውል ሰነድ" ማለት በዚህ ውስጥ የተዘረዘሩ ሰነዶችን ፤አባሪዎችን፤ ማሻሻያዎች እና ማራዘሚያዎችን ያካትታል፤

2.1.3 "አገልግሎቶች" ማለት የድጅታል ቀጠሮ ማስያዣ ፕላት ፎርም አገልግሎት እና ከዚህ ውል ጋር ተያያዥነት ያላቸው የኢሜይል ልውውጦች፣ ሪማይንደሮች ማንኛውም አገልግሎቶች ማለት ነው፡፡

2.1.4 “ውል ዋጋ” ማለት በውሉ ውስጥ የተጠቀሰው አገልግሎት ሰጪው የሚከፈለው ክፍያ ማለት ነው፡፡

2.1.5 "ቀን" ማለት ተከታታይ የቀን መቁጠሪያ ቀናቶች ማለት ነው፡፡

2.1.6 “ማዘግየት” ማለት በውሉ ውስጥ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ስራዎችን ሳያከናውኑ መቅረት ማለት ነው፡፡

2.1.7 “ውል ተቀባይ” ማለት በውሉ ውስጥ በተጠቀሰው መሰረት ማለት ነው፡፡

2.1.8 “ስራ” ማለት የዲጂታል ቀጠሮ ማስያዣ ፕላትፎርም ማለት ነው፡፡

2.1.9 “ውል ሰጪ” ማለት በዚህ ዉል መሰረት አሐዱ ዌብ ዶት ኮም ማለት ነው፡፡

2.1.10 “ሚስጥራዊ መረጃዎች" ማለት የውል ተቀባይ ድርጅት ሚስጥር ነው ተብሎ የታሰቡ መረጃዎች በሙሉ ማለት ነው::

2.1.11 “ግጭት” ማለት ከውል የሚመነጭ ማናቸውም አይነት ክርክር ወይም የይገባኛል ጥያቄዎች ናቸው፡፡

2.1.12 “ከአቅም በላይ የሆነ ችግር" ማለት ሁኔታዎች ወይም ክስተቶች ከተዋዋይ ወገኖች ቁጥጥር ውጪ የሆነ ያልታሰበ፤ሊወገድ የማይችል እና መነሻው በተዋዋይ ወገኖች ቸልተኝነት ወይም ጥንቃቄ በጎደለው ተግባር ባልሆነ እና ተዋዋይ ወገኖች ግዴታቸውን እንዳይወጡ የሚከለክላቸው ሁኔታ ሲሆን እነዚህም ሁኔታዎች ጦርነት ፤ብጥብጥ (አብዮት) ፤እሳት አደጋ ፤ ጎርፍ የመሬት መንቀጥቀጥ ፤ ማዕቀብ በቀጥታ እና ጉዳት ሲያስከትል በሚችል መልኩ የዚህን ውል መፈፀም የሚከለክሉ ሲሆኑ ነው፡፡

አንቀጽ ሦስት

የውል ሰነዶች ዝርዘር

3.1. ከዚህ በመቀጠል የተዘረዘሩት ሰነዶች የዚህ ውል አካል ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡

) ይህ የውል ስምምነት፤

) የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ፤

) የኢሜይል ልውውጦች

አንቀጽ አራት

የውል ስምምነቱ አጠቃላይ ወሰን፤

 

4.1. ውል ሰጪ በዲጂታል ቀጠሮ ማስያዣ ፕላት ፎርም በመጠቀም ታካሚዎች በየትኛውም ግዜ እና ቦታ ሆነው ያለምንም ሰልፍና ወረፋ የውል ተቀባይን የአገልግሎት ቀጠሮ ማስያዝ እንዲችሉ ማስቻል ነው፡፡ በተጨማሪም በዲጂታል ቀጠሮ ማስያዣ ፕላት ፎርም ውል ተቀባይ ያሉትን አገልግሎቶች ማለትም የህክምና አይነቶች፣ የዶክተሮች መረጃ እና የአገልግሎት ክፍያዎችን በውል ሰጪ ፕላት ፎርም መረጃዎችን በማስገባት ለተጠቃሚዎቹ በቀላሉ እንዲታይ እና ቀጠሮ መቀበል እንዲችሉ ማስቻል ነው፡፡

አንቀጽ አምስት

የውል ሰጪ ግዴታዎች

በዚህ ውል የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ውል ሰጪው ከዚህ ቀጥሎ የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩታል፡-

5.1. ውል ሰጪ አገልግሎቱን በተቀላጠፈና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ለውል ተቀባይ በሚፈለገው መጠን እና ጥራት መሰረት አሟልቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

5.2. ለውል ተቀባይ የአጠቃቀም እና የቴክኒካል ድጋፍ ለስራ ባልደረቦች ሁሉ በቪዲዮ የተደገፈ የፕላት ፎርሙ አጠቃቀም እገዛ ያደርጋል፡፡ችግር በሚገጥምበት ጊዜም ባስቸኳይ የቴክኒካል ድጋፍ ያደርጋል፡፡

5.3. ውል ተቀባይ በ15 ቀናት ውስጥ ሽያጭ ካለው ውል ሰጪው የአገልግሎት ክፍያውን 10% ቀንሶ ቀሪውን 90% በየ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለውል ተቀባይ ክፍያ ይፈፅማል፡፡

5.4. ውል ሰጪው ዘመኑን የዋጀ ለተጠቃሚዎች ምቹ እና አስተማማኝ የሆነ የክፍያ ስርዓት መዘርጋት ይኖርበታል፡፡

5.5. ውል ሰጪው ቴክኖሎጂውን ተደራሽ ለማድረግ አስፈላጊ በሆኑት የማስታወቂያ ሚዲያዎች እና የሶሻል ትስስር ገፆች የማስተዋወቅ ስራ ያከናውናል፡፡

5.6. የውል ሰጪው የደንበኞቹን መረጃ በተገቢው መንገድ የመጠበቅ እና ደህንነቱን የማስጠበቅ ኃላፊነት አለበት፡፡

5.7. ውል ሰጪው ከአገልግሎት ያገኘውን የ10% ክፍያ ብቻ የሥራ ግብር ለመንግስት ገቢ ያደርጋል፡፡

5.8. ውል ሰጪው ለተቀበለው 10% ክፍያ ደረሰኝ የመስጠት ኃላፊነት አለበት፡፡

5.9. የውሉ ዋጋ እንዳስፈላጊነቱ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡

5.10. ውል ሰጪው የዋጋ ለውጥ ካለ ከ30 ቀናቶች በፊት ለውል ተቀባይ በኢሜይል ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

አንቀጽ ስድስት

የውል ተቀባይ ግዴታዎች

6. በዚህ ውል የተደነገው እንደተጠበቀ ሆኖ ውል ተቀባይ ከዚህ ቀጥሎ የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩታል፡-

6.1. ውል ተቀባይ በውል ሰጪ በሚቀበለው ቀጠሮ መሰረት ተገልጋዮችን ወይም ታካሚዎችን በቀጠሯቸው መሰረት ያለምንም እንግልት የማስተናገድ ግዴታ አለበት፡፡

6.2. የውል ተቀባዩ ተጨማሪ የቀጠሮ ማስያዣ ክፍያ ከተገልጋዮቹ ወይም ከታካዎቹ ማስከፈል አይችልም፡፡

6.3. የውል ተቀባዩ በውል ሰጪ ፕላትፎርም ላይ የሚያስገባቸው መረጃዎች፣ አገልግሎቶች፣ ክፍያዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ዶክተሮች የራሱ እና ትክክኛነቱን የማረጋገጥ ኃላፊነት የራሱ ይሆናል፡፡ ይህ ሆኖ ሳይቀር ለሚፈጠረው የተዛባ እና ሀሰተኛ መረጃ ለሚፈጠረው ችግር እና ጥፋት ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡

6.4. ውል ተቀባይ የአገልግሎት ለውጥ ወይም የክፍያ ለውጥ የማድረግ ሙሉ መብት አለው፡፡

6.5. ውል ተቀባይ የሥራ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ ሊኖረው ይገባል፡፡ ይህ ሆኖ ሳይቀር ለሚፈጠረው ችግር ውል ሰጪው ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡

6.6. ውል ተቀባይ በንግድ ፍቃድ እና በንግድ ስያሜ የተፈቀደለትን አገልግሎቶች ብቻ በውል ሰጪ ፕላትፎርም አገልግሎቱን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ሆኖ ሳይቀር ለሚፈጠረው ችግር ውል ተቀባይ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡

6.7. የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ወይም ታካሚዎች በወቅቱ አገልግሎት በሚሰጥበት ተቋም ባይደርሱ እስከ 30 ደቂቃ የመጠበቅ ግዴታ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም ውል ተቀባይ በተለያየ ምክንያቶች አገልግሎት ለመስጠት ቢዘገይ ታካሚው እስከ 30 ደቂቃ መጠበቅ ይኖርበታል፡፡

6.8. ታካሚው ቢቀር ወይም የቀጠሮ ለውጥ ካደረገ ውል ተቀባይ በተለዋጭ ቀጠሮ ለ3 ወር ያልበለጠ በተለዋጭ ቀጠሮ የማስተናገድ ኃላፊነት አለበት፡፡

6.9. ውል ተቀባይ ለተከፈለ ቀጠሮ ተመላሽ አያደርግም፡፡

6.10. ውል ተቀባይ ለታካሚው አስፈላጊውን ደረሰኝ የመቁረጥና የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

6.11. ሁሉም ክፍያ የሚከፈለው በኢትዮጵያ ብር ይሆናል፡፡

አንቀጽ ሰባት

ግብር

7. ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች በህግ የሚጣልባቸውን ማንኛውንም አይነት ግብር የመክፈል ግዴታ አለባቸው፡፡

አንቀጽ ስምንት

የውል ስምምነት ማሻሻያ እና ማስተካከያ

8.1. ይህ ውል በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት ሊሻሻል እና ሲስተካከል ይችላል፤

8.2. ምንም አይነት ማሻሻያ ወይም ማስተካከያ በሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ካልተፈፀመ፤ በፅሁፍ ካልሆነ፤ቀን ካልተፃፈበት እና ዋናው ውል ካልተጠቀሰ በስተቀር እንደ ማሻሻያ ሊወሰድ አይችልም

 

አንቀጽ ዘጠኝ

ተግባራዊ የሚሆኑ ህጎች

9. ይህ ውል የሚመራውም ሆነ የሚተረጎመው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ባወጣቸው እና በሚተገብራቸው ህጎቾ መሰረት መሆኑን እንዲሁም ክርክር ቢነሳ አግባብነት ባላቸው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊሪፐብሊክ መንግስት ፍርድ ቤቶች የሚዳኝ ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስር

ቋንቋ

10. ይህን ውል በተመለከተ በውል ሰጪው እና በውል ተቀባይ መካካል የሚኖሩ ማናቸውም አይነት ግንኙነቶች በፅሁፍ እና በአማርኛ መሆን እንዳለባቸው ተዋዋይ ወገኖች ተስማምተዋል፡፡

አንቀጽ አሥራ አንድ

የግጭት አፈታት

11. ተዋዋይ ወገኖች ግጭቶቻቸን በመቀራረብ እና በመነጋገር መፍታት አለቸው ነገር ግን በ15 ቀናት ውስጥ ግጭቶቻቸን በመግባባት መፍታት ካልቻሉ አንደኛው ተዋዋይ ወገን ጉዳዩን ስልጣን ወደ አለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት መሙሰድ ይችላል፡፡

አንቀጽ አሥራ ሁለት

የውል ስምምነቱ የሚፈርስባቸው ምክንያቶች፤

12.1 በአሐዱ ዌብ ዶት ኮም በኩል ውል ሰጪው የ15 ቀን የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ሊያቋርጥ የሚችለው፡-

) ውል ተቀባይ ደንበኞችን በቀጠሯቸው ጊዜ እና በተገቢው መንገድ ሳያስተናግድ ሲቀር፡፡

) ውል ተቀባይ ተጨማሪ የቀጠሮ ማስያዣ ክፍያ የሚጠይቅና የሚያስከፍል ከሆነ፡፡

) ውል ተቀባይ ለተቀበለው ቀጠሮ አገልግሎቱን መስጠት ሳይችል ሲቀር፡፡

) ውል ተቀባይ ደንበኞችን በማጉላላት እና ቀጠሮዎችን ከአንድ በላይ እሚቀይር ሆኖ ሲገኝ

) ውል ተቀባይ በውሉ ውስጥ የተጠቀሱ ግዴታዎቹን ሳይወጣ ሲቀር።

) ውል ተቀባይ የሚጠበቅበትን አገልግሎት በተገቢው መንገድ ሳይሰጥ ሲቀር፡፡

) ውሉ እንዳይፈፀም የህግ ክልከላ ሲኖር

12.2 በውል ተቀባይ ሲቋረጥ፤- ውል ተቀባይ የ15 ቀን ቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት ሊያፈርስ ይችላል፡-

) ውል ሰጪ በውሉ ውስጥ የተመለከተውን ግዴታ በትክክል ሳይወጣ ሲቀር።

) ጉድለቱን እንዲያስተካክል ውል ተቀባይ ገልጾለት ሳያስተካክል ሲቀር።

) ውል ሰጪ የሰበሰባቸውን ክፍያዎችን በወቅቱ ሳይከፍል ሲቀር፡፡

) ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ውል ተቀባይ ግዴታውን መወጣት ሲያቅተው።

) የውል ሰጪ የቴክኒካል ድጋፍ አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ እገዛ ሳያደርግ ሲቀር፡፡

) ውል ተቀባይ በራሱ ፈቃድ የ15 ቀን የፅሁፍ ማስንቀቂያ በመስጠት ሊያቋርጥ ይችላል፡፡

አንቀጽ አሥራ ሶስት

ውል ማሻሻያ

13.1. ውል ሰጪ ይህን ውል አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የማሻሻል ሙሉ መብት አለው፡፡

13.2. የተሻሻለውን ውል ለውል ተቀባይ በዲጂታል ቀጠሮ ማስያዣ ፕላትፎርም ዌብሳይት እና በውል ተቀባይ ባስመዘገበው ኢሜይል የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡

አንቀጽ አሥራ አራት

የውሉ ተፈፃሚነት

14. ውሉ መፈፀም የሚጀምረው ውል ተቀባይ ውሉን ከፈረመበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡

አንቀጽ አሥራ አምስት

ውሉ የሚፀናበት ጊዜ

15. ይህ ዉል በሁለቱ ወገኖች ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን ከሁለቱ ተዋዋዮች ባንዱ ወይም ከሁለቱ ወገን እስካልፈረሰበት ወይም በውል ሰጪ አካል ውሉን እስካላሻሻለበት ድረስ ውሉ የፀና ይሆናል፡፡

አንቀጽ አሥራ ስድስት

የውሉ ህጋዊነት



16.1 ይህ ውል በውስጡ ላለው ቃል ለሚፈጠረው መብትና ግዴታ ግራ ቀኝ ተወያይተን በፍ///1731 እና 2005 መሰረት ህግ አድርገን በመቀበል በፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡

16.2. በዚህ ውል አገልግሎት ሰጪው አንቀፅ 2 ላይ የተዘረዘሩት የውል ሰነዶች እና የልውውጥ ኢሜይሎች የውሉ አካል ተደርገው በተጨማሪም አግባብነት ባላቸው የአገራችን ፍትሐብሔር ህጎች ይሸፈናሉ፡፡

 

ይህ ውል ከዛሬ ቀን May 27, 2026 .ም በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች ምስክሮች ባሉበት ተፈርሟል፡፡





ውል ተቀባይ

ስም  

ስልክ  

ቀን May 27, 2026

Leave this empty:

Signature arrow


Signature Certificate
Document name: የጤና ፈርስት የውል ስምምነት
lock iconUnique Document ID: d5115d731843d60c4d221b0b0a23a98423ea279e
Timestamp Audit
August 2, 2023 12:28 pm EATየጤና ፈርስት የውል ስምምነት Uploaded by Misgana Haile - account.m@ahaduweb.com IP 196.188.35.138
August 2, 2023 12:34 pm EATTenaFirst Agreement - agreement@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 12:34 pm EATMeles Worku - telebirr@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 1:48 pm EATTenaFirst Agreement - agreement@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 1:48 pm EATMeles Worku - telebirr@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 1:49 pm EATTenaFirst Agreement - agreement@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 1:49 pm EATMeles Worku - telebirr@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 2:08 pm EATTenaFirst Agreement - agreement@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 2:08 pm EATMeles Worku - telebirr@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 2:11 pm EATTenaFirst Agreement - agreement@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 2:11 pm EATMeles Worku - telebirr@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 2:13 pm EATTenaFirst Agreement - agreement@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 2:13 pm EATMeles Worku - telebirr@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 2:15 pm EATTenaFirst Agreement - agreement@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 2:15 pm EATMeles Worku - telebirr@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 4:11 pm EATTenaFirst Agreement - agreement@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 4:11 pm EATMeles Worku - telebirr@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 4:41 pm EATTenaFirst Agreement - agreement@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 4:41 pm EATMeles Worku - telebirr@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 4:41 pm EATTenaFirst Agreement - agreement@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 4:41 pm EATMeles Worku - telebirr@tenafirst.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 5:25 pm EATTenaFirst Agreement - agreement@ahaduweb.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 5:25 pm EATMeles Worku - telebirr@ahaduweb.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 5:35 pm EATTenaFirst Agreement - agreement@ahaduweb.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 2, 2023 5:35 pm EATMeles Worku - telebirr@ahaduweb.com added by Misgana Haile - marketing.team2@tenafirst.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 3, 2023 1:45 pm EATTenaFirst Agreement - agreement@ahaduweb.com added by Misgana Haile - account.m@ahaduweb.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 3, 2023 1:45 pm EATMeles Worku - telebirr@ahaduweb.com added by Misgana Haile - account.m@ahaduweb.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 7, 2023 10:07 am EATTenaFirst Agreement - agreement@ahaduweb.com added by Misgana Haile - account.m@ahaduweb.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 7, 2023 10:07 am EATMeles Worku - telebirr@ahaduweb.com added by Misgana Haile - account.m@ahaduweb.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 7, 2023 11:12 am EATTenaFirst Agreement - agreement@ahaduweb.com added by Misgana Haile - account.m@ahaduweb.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15
August 7, 2023 11:12 am EATMeles Worku - telebirr@ahaduweb.com added by Misgana Haile - account.m@ahaduweb.com as a CC'd Recipient Ip: 196.188.35.15